“በምርጫ የተገባውን ቃል በላቀ አፈጻጸም ማረጋገጥ ይገባል” አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)

5

 

የምሥራቅ አማራ ቀጣና ከፍተኛ እና መካከለኛ መሪዎች በወቅታዊ የሰላም እና የልማት ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው።

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ከምርጫ ማግስት መሪዎች በተሟላ አቅም የልማት እና የሰላም ሥራዎችን በመፈጸም ለሕዝብ የተገባውን ቃል መፈጸም እንደሚገባ አሳስበዋል።

በክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስፋት፤ የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት የዜጎችን ገቢ ማሳደግ፤ ተቋማት ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባም ነው ዶክተር አብዱ የተናገሩት።

የክልሉን ሰላም በማረጋገጥ የተሠሩ ሥራዎች አበረታች ናቸው ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ የክልሉን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የተጀመረው የሕግ ማስከበር እና የማኅበረሰቡን ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የሥራ ኀላፊዎች የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ከማኅበረሰቡ እና ቀበሌ መዋቅሩ ጋር መግባባት እንደሚገባ ነው ዶክተር አብዱ ያሳሰቡት።

#አማራ_ክልል #አመራር_ምክክር #ሰላምና_ልማት #ህግ_ማስከበር #የበጎ_ፈቃድ_አገልግሎት #AmaraRegion #Ethiopia
#ደሴ: #ሰኔ28/2018ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleሊማሊሞ አስደናቂው ሥፍራ 🏔️✨
Next article🔥 መከላከያ ሠራዊት ዛሬም እንደትናንቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የማጽናት አቋም ላይ ነው”🔥 🇪🇹