
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሀገርን ሰላም እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ምርጫው በስኬት መካሄድ አለበት።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም፣ በነጻነት እና በፍትሐዊነት እንዲጠናቀቅ ማድረግ ደግሞ ከጸጥታ ኃይሉ በእጅጉ ይጠበቃል።
የሰሜን ጎንደር ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ዳኝነት ሙሉሰው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ እና ፍትሐዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል።
የምርጫ ቁሳቁስ ከዋናው ማዕከል ወደ ዞን እና ወደ ወረዳ ማዕከላት ሲጓጓዝ አስፈላጊው ጥበቃ
እየተደረገ እንደኾነም አንስተዋል።
“ለምርጫው ስኬታማነት ማኅበረሰቡ ከሰላም ጎን ኾኖ ኀላፊነቱን እየተወጣ መኾኑንም” አንስተዋል።
ሰላማዊ በኾነ መንገድ እና በዜጎች ፍትሐዊ ድምጽ የተቋቋመ ሕጋዊ መንግሥት እንዲኖር ማኅበረሰቡ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
#ምርጫ #ሰሜን ጎንደር #አማራ #ኢትዮጵያ🇪🇹
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
