
ባሕር ዳር: ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ግዙፉ የቦረና የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ፕሮጀክት ለኅብረተሰቡ አስተማማኝ የንጹሕ ውኃ አቅርቦት ተደራሽ በማድረግ፣ በምሥራቅ ቦረና እና በቦረና ዞኖች የሚገኙ ነዋሪዎችን ሕይወት እየቀየረ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በብዙ ኪሎ ሜትሮች የሚቆጠሩ የቧንቧ መስመሮችን፣ ዘመናዊ የውኃ ማከፋፈያ ጣቢያዎችን እና ሰፋፊ የውኃ ማጠራቀሚያዎችን ያካተተ ዘላቂ መሠረተ ልማት እየተገነባ ሲኾን ይህም ድርቅን ለመመከት የላቀ ፋይዳ እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመላክተዋል።
በተጨማሪም በፕሮጀክቱ የሕዝብ ጤናን የመጠበቅ፣ የነዋሪዎችን መተዳደሪያ አቅም የማጠናከር እና መጭው ትውልድ የሚጠቀምበትን የግብርና እምቅ አቅም የማዘጋጀት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ነው የገለጹት።
#አሚኮ_ዜና #የልማት_ሥራ #ቦረና #ኢትዮጵያ🇪🇹
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
