
አዲስ አበባ: ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች ተከብሯል።
በዓሉን ሲያከብሩ ካገኘናቸው መካከል ኡስታዝ ጀማል በሽር ለሀገር እና ለማኅበረሰብ መሰረት የኾነው ቤተሰብ በነብዩ ኢብራሒም እና በልጁ ነብዩ ኢስማኤል በአላህ የተሰጣቸውን የመታዘዝ ፈተና በማለፋቸው መስዋዕቱን በግ አደረገላቸው፤ ይህም “መታዘዝን በተግባር ያስተማረ ነው” ብለዋል።
ሌላው ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት ሼህ መሐመድ ቃሲም ልጅ አባቱን እንዲታዘዝ አረፋ ትልቅ ተምሳሌት ነው ብለዋል። ታናሽ ታላቅን ማክበር፤ ታላቅ ታናሽን ማድመጥ ዋጋው ለአላህ እንደሚሰማ ያስተማረ በዓል እንደኾነም ገልጸዋል።
በአረፋ ተራራ መስዋዕትነት ከትዕዛዝ ጋር ተጣምሮ፤ ቃልም በእምነት ታስሮ የተገለጠበት ምስጢር ዛሬ ላይ ለሀገር መስዋዕትነት መክፈል አስፈላጊ እንደኾነ የምንማርበት በዓል አረፋ መኾኑን ነው የገለጹት።
እስልምና ከመስዋዕትነት ባለፈ ሰላምን የሚያስተምር በመኾኑ ለሰላም መሥራት እንደሚገባ ያነሱት ደግሞ ከድር ለገሰ ናቸው።
ምስኪን ብዙ አይነት ነው፤ ሳይኖረው መጠየቅ የሚፈራ በአካባቢያችን ያለ በመኾኑ ሁሉንም ቃኝቶ የአላህን ትዕዛዝ በጠበቀ መልኩ በዓሉን ማክበር እጅግ አስፈላጊ መኾኑንም የበዓሉ ተሳታፊዎች አንስተዋል።
#አሚኮ #ኢድአልአድሃ #አዲስአበባ #ኢትዮጵያ
ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
