ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ አሚኮ በደሴ ከተማ እያስገነባው የሚገኘውን የሚዲያ ኮምፕሌክስ ጎበኙ።

9

 

ደሴ፡ ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ አሚኮ በደሴ ከተማ እያስገነባው የሚገኘውን የሚዲያ ኮምፕሌክስ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን ( ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በደሴ ከተማ እያስገነባው የሚገኘው ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

ባለ 14 ወለል ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ነው። ዘመናዊ የሚዲያ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም እና ትልቅ ገንዘብ የሚጠይቅም ግንባታ ነው።

ለምሥራቅ ቀጣና የሚዲያ ማዕከል ኾኖ እንዲያገለግል እና የአሚኮን ተደራሽነት የሚያሰፋ ነው።

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አስቻለ አየሁዓለም የአሚኮ የደሴ የሚዲያ ኮምፕሌክስ በጥሩ አፈጻጸም ላይ መኾኑን ገልጸዋል።

በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል። የግንባታው አፈጻጸም በተከታታይ እየተገመገመ አቅጣጫ እየተቀመጠበት እየተመራ መኾኑን አንስተዋል።

የሲቪል ሥራው ተጠናቆ የፊኒሽንግ ሥራዎች እየተሠሩለት መኾኑን ገልጸዋል። የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተደራሽነቱን ለማስፋት የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ መኾኑን ተናግረዋል። የደሴው የሚዲያ ኮምፕሌክስ ለቀጣናው የሚዲያ ማዕከል ኾኖ እንደሚያገለግል አንስተዋል።

የሚገጠምለት የሚዲያ ቴክኖሎጂም ዘመናዊ መኾኑን ተናግረዋል። የሚዲያ ኮምፕሌክሱ የአሚኮን ተወዳዳሪነት የበለጠ እንደሚያሳድገው ገልጸዋል። ለተወዳዳሪነት ደግሞ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና የሚዲያ ግንባታ አስፈላጊ መኾኑን ተናግረዋል።

የግንባታ ሥራውን እየሠራው ያለው የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ታደሰ ግርማ የሚዲያ ኮምፕሌክሱ ጥራቱን ጠብቆ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል። ሥራውን በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ እንደሚሠራም አንስተዋል።

የማጠናቀቂያ ግብዓቶችም እየቀረቡ መኾናቸውን ተናግረዋል። ሥራውን ለማጠናቀቅ በመወያየት የጋራ አቅጣጫ ተቀምጧል ነው ያሉት።

ዘጋቢ፦ ታርቆ ክንዴ

#አሚኮ #ልማት #ኢትዮጵያ #ደሴ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“የምርጫው ቀን ሕዝባችን ያለምንም ስጋት ድምጽ የሚሰጥበት ታሪካዊ ቀን እንዲኾን እናደርጋለን” ኮሚሽነር ጄኔራል ዘላለም መንግሥቴ (ዶ.ር)
Next articleየጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልእክት