በዓሉን ለሀገር ሰላም እና አንድነት በመጸለይ ማክበር ይገባል።

8

 

ደብረ ማርቆስ: ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 1ሺህ 447ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በደብረ ማርቆስ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ተከብሯል።

በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የታላቁ ቢን አፊፍ መስጊድ ኢማም ሼህ መሐመድ ሽፋው ፤ አረፋ አንድነትን፣ ፍቅርን እና መተሳሰብን የምንማርበት ታላቅ በዓል ነው ብለዋል። በመኾኑም በዓሉን በመረዳዳት እና የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ማክበር እንደሚገባም አሳስበዋል።

በበዓሉ ላይ የተገኙት የምሥራቅ ጎጃም ዞን ሸሪያ ፍርድ ቤት ዳኛ ሼህ ወለላው ሰይድ ሕዝበ ሙስሊሙ የአረፋ በዓልን ሲያከብር የሃይማኖቱ አስተምህሮን በመከተል እና በመተግበር ሊኾን እንደሚገባ ገልጸዋል።

በዓሉን ለሀገር ሰላም እና አንድነት በመጸለይ ማክበር እንደሚገባም አሳስበዋል።

የአረፋ በዓል አማኞች እርስ በእርስ የምንጠያየቅበት እና መልካም ምኞታችንን የምንለዋወጥበት ከመኾኑም ባለፈ ለተቸገሩ ወገኖች ያለንን የምናካፍልበት ነው ያሉት ደግሞ የበዓሉ ታዳሚዎች ናቸው።

#አሚኮ_ዜና #ዓረፋ #ዒድ_አል_አደሃ #ደብረማርቆስ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“ዘመናትን የተሻገረ የማኅበረሰቡ አብሮነት ለዛሬዋ የጎንደር ከፍታ ዋነኛ መሠረት ኾኗል” አቶ ቻላቸው ዳኘው
Next article“ደሴ ከተማን ወደ ላቀ ከፍታ ማማ ለመውሰድ በሚደረገው ጉዞ ሕዝቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀርባለሁ” አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ