
አዲስ አበባ: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደረው ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የማጠቃለያ መርሐ ግብሩን አካሂዷል።
በምርጫ ቅስቀሳው ላይ የፓርቲው አባላት፣ ደጋፊዎች እና የፓርቲው መሪዎች ተገኝተዋል።
የፓርቲው ፕሬዝዳንት አብርሐም ጌጡ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ በሰላማዊ ትግል እንደሚያምን ገልጸዋል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በንቃት እየተሳተፉ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
ፓርቲው ሀገራዊ አንድነትን የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎችን መቅረጹን እና በተዘጋጁ የምርጫ ክርክሮች ላይ ሲያቀርብ መቆየቱንም አንስተዋል።
ዜጎች በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ይኾነኛል ያሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ያወጡትን ካርድ በምርጫው ዕለት እንዲጠቀሙበትም ፓርቲው አሳስቧል።
ዘጋቢ፦ አልሳ ጉኡሽ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
