
ባሕር ዳር :ግንቦት 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የመድረኩ ተሳታፊዎቹ በካርዳቸው የሚመራቸውን ፓርቲ ለመምረጥ በጉጉት እየተጠባበቁ መኾኑን ገልጸዋል።
የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ደበበ አክሎግ ፓርቲያቸው ቃሉን በተግባር ለመተርጎም ቁርጠኛ መኾኑን ገልጸዋል።
የከተማ አሥተዳደሩ ከንቲባ ደሴ መኮንን በመድረኩ ላይ እንደገለጹት ሀገራዊ ምርጫ ማስኬድ የሕልውና ጉዳይ ሲኾን፣ ሥርዓት አልበኝነትን ለማስወገድ ዋነኛው አማራጭም ፍትሐዊ እና ሰላማዊ ምርጫ ማካሄድ ነው።
ለምርጫው ስኬታማነት የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ድምፃቸውን ከመስጠት ባለፈ፣ ምርጫውን ለማደናቀፍ ግጭት የሚፈልጉ አካላትን በመምከር ረገድ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ አማካሪ ባየ አለባቸው አባቶች ሀገር እንድትቀጥል ያላቸውን ታሪካዊ ኀላፊነት በመወጣት፣ የምርጫን አስፈላጊነት ተረድተው በሕዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለውን ፓርቲ ለይተው መምረጥ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
