ባሕር ዳር: ሚያዝያ 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በባሕርዳር ዙሪያ መሸንቲ አካባቢ የሀገር ኩራት የሆነው የምሥራቅ ዕዝ ኮር አንድ ሬጅመንት ባደረገው ስኬታማ ኦፕሬሽን የፅንፈኛዉን የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎችን መማረኩ ታውቋል።
የሬጅመንቱ የሠራዊት አባላት በቆራጥነትና በላቀ የውጊያ ስልት በወሰዱት እርምጃ የታጣቂ ቡድኑ መትረየስ (ብሬን) ከነሸንሸሉ እና አምስት ክላሽን ከነ ተተኳሹ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ ምሥራቅ ዕዝ አስታውቋል።
የሬጅመቱ መሪ ሻንበል ጌትነት አለሙ እንደገለፁት ይህ ስምሪት የሠራዊቱን ዝግጁነትና የማድረግ አቅም በግልጽ ያሳየ ሲሆን በኦፕሬሽኑ ወቅት የሬጅመንት አባላቱ ያሳዩት ቅንጅትና ተጋድሎ የሚደነቅ እንደነበር ተናግረዋል።
ሬጅመንቱ ጠላትን በመደምሰስና የጥፋት ኀይሎችን ሴራ በማምከን የአካባቢውን ሰላም ይበልጥ አስተማማኝ ማድረግ መቻሉ ተመልክቷል። መረጃው የምሥራቅ ዕዝ ነው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
