በደሃና ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ18 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

8

 

ባሕር ዳር ሚያዝያ 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ደሃና ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ18 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

መነሻውን እብና ከተማ አድርጎ መዳረሻውን ሰቆጣ ከተማ ያደረገው አይሱዙ በመጓዝ ላይ እያለ ልዩ ቦታው ደሃና ወረዳ 09 ቀበሌ ድግሽዋ በሚባል ቦታ የትራፊክ አደጋ ደርሶበታል፡፡ በአደጋውም 18 ሕይወታቸው አልፏል፡፡ 62 ሰዎች ለከባድ እና ቀላል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡

በደሃና ወረዳ አምደወርቅ ጤና ጣቢያ እና አምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሕክምና አገልግሎት እየተሰጣቸው መሆኑን የደሃና ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) በደረሰው አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ፣ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን፣ ለተጎጂዎች ደግሞ ፈጣን ምሕረትን ይመኛል።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አንድ ተቋም የተሳካ የመዋቅር ለውጥ ሲያደርግ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈጸም ያስችለዋል” አቶ ዓለምአንተ አግደው