በአማራ ክልል ከ896 በላይ አነስተኛ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።

16
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጂ ቢሮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት እየገመገመ ነው።
የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኀላፊ ኢንጅነር ዳኝነት ፈንታ (ዶ.ር) ባለፉት ዘጠኝ ወራት እንደ ተቋም የንጹሕ መጠጥ ውኃ፣ የሳኒቴሽን መሠረተ ልማት ግንባታ እና የታዳሽ ኢነርጂ ልማት ላይ ሰፊ ሥራዎች ሲሠሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል። በዚህም ካለፉት ዓመታት አንጻር የተሻለ አፈጻጸም እንደተመዘገበ ነው የጠቀሱት።
ለአብነትም በመጠጥ ውኃ ዘርፍ ከ896 በላይ የሚኾኑ አነስተኛ ተቋማትን ማጠናቀቅ እንደተቻለ ገልጸዋል። በከፍተኛ እና በመካከለኛ ደግሞ እየተሠሩ ካሉ 80 በላይ ፕሮጀክቶች 24 በላይ የሚኾኑትን ማጠናቀቅ መቻሉን ጠቅሰዋል።
ዛሬ እየተደረገ ያለው ግምገማ የነበሩ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እና ውስንነት የተስተዋለባቸውን ተግባራት በቀሪ ወራት ለመፈጸም ያለመ መኾኑንም አንስተዋል።
በግምገማው በፕሮጀክት አፈጻጸም የገጠሙ ችግሮችን በመፍታት የሚገነቡ ተቋማት ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ በኩል የተጀመሩ ሥራዎችን ማጠናከር እና የአገልግሎት ተደራሽነትን ማስፋት ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል።
ከዚህ ባሻገር የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን ማረም እና የሀብት አጠቃቀምን መፈተሽም ትኩረት የሚደረጉባቸው ጉዳዮች ናቸው ተብሏል።
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በአፍሪካ ኅብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ ሆነው ተሾሙ።
Next articleሪፎርሙ የመንግሥት ሠራተኞችን ይቀንሳል?