
አዲስ አበባ: መጋቢት 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ መጋቢት 9/2018 ዓ.ም ከታየች ነገ ሐሙስ መጋቢት 10/2018ዓ.ም፤ ካልታየች ደግሞ መጋቢት 11/2018 ዓ.ም እንደሚውል የፌዴራል የጠቅላይ ሸሪአ ፍርድ ቤት ገልጿል።
መተዛዘን እና በችግሮች ሁሉ አብሮ መቆም ከኢዱም በኋላ ሊቀጥል እንደሚገባ የገለጸው ደግሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነው።
ምክር ቤቱ ኢድ አል ፈጥር በዓልን አስመልክቶ የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፏል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ አብዱልከሪም ሼህ በድረዲን ረመዳን የዕዝነት፣ የመረዳዳት፣ የፍቅር እና የሰላም ወር በመኾኑ ይህንን ተግባር ከበዓሉ በኋላም ማስቀጠል ይገባናል ብለዋል።
በጋሞ የተፈጠረው አደጋ ልባችንን ሰብሮታል፤ አዝነናል ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ተጎጅዎችን ከጎናቸው ኾነን መርዳት ይኖርብናል ነው ያሉት።
ዘካትል ፊጥር በወቅቱ በማውጣት ከተቸገሩ ወገኖችን
ጎን መቆም እንደሚገባ አሳስበዋል።
በዓሉ የሚውልበትን ቀን አስመልክቶ ጠቅላይ ሸሪአ ፍርድ ቤቱ በሰጠው መግለጫ የኢድ አልፈጥር በዓል ጨረቃ ዛሬ መጋቢት 9 ማታ ከታየች ሐሙስ መጋቢት 10/2018 ዓ.ም፣ ካልታየች ደግሞ አርብ መጋቢት 11/2018 ዓ.ም ይከበራል ብሏል።
ዘጋቢ: ድልነሳ መንግሥቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
