“ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የጽናት ሽልማት ነው” ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

12
ባሕር ዳር: ጳጉሜን 4/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የጽናት ሽልማት መኾኑን ተናገሩ።
ፕሬዝዳንቱ የግድቡን መመረቅ ተከትሎ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ ግድቡ የኢትዮጵያውያን የላብ፣ የደም እና የእንባ ውጤት ነው ብለዋል።
ያለፉት እና አሁን ያሉት መሪዎች ግድቡ እውን እንዲኾን ለሰነቁት ራዕይ እና ላሳዩት ድፍረት እናመስግናን በማለት ገልጸዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የፅናት ሽልማት ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ግድቡ የዓባይ ልጆችን ከብዙ በረከት ጋር የሚያስተሳስር መኾኑንም ተናግረዋል፡፡
ግድቡ ዘላቂ የዕድገት ብርሃንን ይዞ እንዲመጣም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“አታልቅስ ይሉኛል ላልቅስ እንጅ አምርሬ ዕዳ በበዛባት፤ ፈተና ባፀናት ሀገር ተፈጥሬ”
Next articleየባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ጳጉሜ 4 “የማንሰራራት ቀን”ን በመሠረተ ልማት ጉብኝት እያከበረ ነው።