የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልዕክት፦

83
በቬይትናም የቶዮ የፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫ ፋብሪካ በነበረን ጉብኝት እና ከኩባንያው ፕሬዝደንቱ ጋር በነበረን ውይይት የፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫዎችን በሀገራችን ለማምረት ተስማምተን ነበር። ዛሬ በሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ በነበረን ጉብኝት በፓርኩ ከፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጪያዎችን እያመረቱ በመመልከታችን ደስታ ተሰምቶናል።
ማምረቻው በከፍተኛ ጥራት ከፍተኛ ምርት የማምረት አቅም የተላበሰና በዘመናዊ የማሽን ሥርዓት የሚሰራ ሲሆን የምርት ውጤቱ ለማኑፋክቸሪንግ የውጪ ንግድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል። ሁለት ተጨማሪ ማምረቻዎች በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ ሲሆን ወደ ምርት የገባውን ማምረቻ ሥራ ሂደት ተመልክተናል። ይኽ ሥራ እሴት የተጨመረባቸው እና ያስቀመጥናቸውን ግቦች እና ፖሊሲዎች የሚያሳኩ ጨዋታ ቀያሪ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት ከሚያደርገው የኢንቨስትመንት ስትራቴጂያችን ጋር የተጣጣመ ነው።

Previous articleለትምህርት የደረሱ ሕፃናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲገቡ እና ትምህርታቸውን ያቋረጡም እንዲመለሱ ጥሪ ቀረበ።
Next articleበተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ63 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።