በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኖቲንግሃም ፎረስት በሜዳው ሲቲ ግራውንድ ቼልሲን 3 ለ 2 በኾነ ውጤት አሸንፏል።
ለባለሜዳው ኖቲንግሃም ፎረስት ብራዚላዊው አጥቂ ኢጎር ጄሱስ በ5ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ድንቅ ግብ ቀዳሚ ሲኾን፣ ሞርጋን ጊብስ-ዋይት በ51ኛው (በፍጹም ቅጣት ምት) እና በ72ኛው ደቂቃዎች ላይ ሁለት ግቦችን በማከል የቡድኑን ድል አረጋግጧል።
በአንጻሩ በአሠልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የሚመራው ቼልሲ ተቀይሮ በገባው ኢሜጋ አማካኝነት በ54ኛው እና በ89ኛው ደቂቃዎች ላይ ሁለት ግቦችን ቢያስቆጥርም ከሽንፈት ሊድን አልቻለም።
ይህ ውጤት ለቼልሲ በፕሪሚየር ሊጉ ተከታታይ ሦሥተኛ ሽንፈት ሲኾን፣ ቡድኑ በ12 ጨዋታዎች 23 ግቦችን በማስተናገድ ከፍተኛ የመከላከል ችግር ውስጥ ይገኛል።
በአሠልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር የሚመራው ኖቲንግሃም ፎረስት በዚህ ድል ከ17ኛ ወደ 14ኛ ደረጃ ከፍ ሲል፣ ቼልሲ ባለበት 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ፎረስት በሜዳው ቼልሲን ሲያሸንፍ ከ1997 እ.ኤ.አ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_19_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



