ባሕር ዳር ከተማ ወይስ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ?

0
82

ባሕር ዳር ከተማ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ4ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ዛሬ ይገናኛሉ።

ሁለቱ ቡድኖች ከ2011 ጀምሮ የግንኙነት ታሪክ ያላቸው ሲኾን በዛሬው ጨዋታም አንዱ ሌላውን አሸንፎ ለመውጣት ከባድ ፉክክር ያደርጋሉ።

የጣና ሞገዶቹ ዛሬ በሜዳቸው እና በደጋፊያቸው ፊት የሚጫዎቱ ቢኾንም ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሚጠብቃቸው ፈተና ቀላል አይኾንም።

ባሕር ዳር ከተማ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3 ለ 1 ማሸነፋቸው ለዛሬው ጨዋታ ጥሩ የስነልቦና መነቃቃት እንደሚፈጥርላቸው ይጠበቃል።

ዛሬ 10፡00 ላይ በባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_16_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here