የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በሊቨርፑል የ4 ለ 0 ሽንፈት የጀመሩት ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ዛሬ ምሽት 5፡00 በስታዲዮ ሆዜ አልቫላድ ሌላ ፈተና ይጠብቃቸዋል።
ማንቸስተር ዩናይትድ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ከአራት ጨዋታዎች ሁለቱን በማሸነፍ በስድስት ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ ቢገኝም፣ በፕሪሚየር ሊጉ አንድ ድል ብቻ በማስመዝገብ የወራጅ ቀጣና (19ኛ ደረጃ) ላይ ተቀምጧል። በሻምፒዮንስ ሊጉ ለመቀጠል እና ወደ ጥሎ ማለፉ ለማለፍ ዩናይትድ ከቀሪ ሁለት ጨዋታዎች ውጤት ይፈልጋል።
በተቃራኒው ዘጠኝ ነጥብ (3 ድል) ይዞ 12ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ስፖርቲንግ፣ ባለፉት 14 ጨዋታዎቹ በሁሉም ላይ ግብ ማስቆጠር ችሏል።
በውድድር ዓመቱ በሁሉም ውድድሮች 34 ግቦች የተቆጠሩበት ዩናይትድ፣ ባለፉት አምስት ጨዋታዎች 15 ግቦችን አስተናግዶ አንዱን ብቻ ሲያሸንፍ፣ በአምስት ጨዋታዎች ያሸነፈው ስፖርቲንግ በአራቱ ግብ ሳይቆጠርበት ወጥቷል።
በፕሪሚየር ሊጉ ለ40 ዓመታት ያልታየውን የወራጅ ቀጣና ጉዞ ለመቀየር፣ የሊቨርፑልን ሽንፈት ለማስረሳት እና በዘንድሮው ሻምፒዮንስ ሊግ ያልተሳካለትን የሜዳ ውጪ ድል ለማግኘት ይህ ጨዋታ ለዩናይትድ ትልቅ ፋይዳ አለው።
የዛሬ ምሽት ሌሎች የሻምፒዮንስ ሊግ መርሐ ግብሮች ሲካሄዱ፦
ምሽት 2፡45 ሳባህ ከ ባርሴሎና እና ስላቪያ ፕራግ ከ ቪያሪያል ጨዋታቸውን ሲያደርጉ
ምሽት 5፡00 ደግሞ ፒኤስጂ ከ ሮማ፣ ክለብ ብሩጅ ከ ሊቨርፑል፣ ሊል ከ ባየርሙኒክ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ቫይኪንግ፣ ሻካታር ዶኔስክ ከ ፌነርባቼ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



