ካፍ የ2026 የዓመቱ ምርጥ የመጨረሻ ተጫዋቾችን ይፋ አድርጓል።
ሦሥት የሞሮኮ እና ሁለት የሴኔጋል ተጫዋቾች ለዓመቱ ምርጥ ተጫዋችነት የመጨረሻ እጩ ኾነው በካፍ ቀርበዋል።
ሃኪሚ፣ ማኔ፣ ብራሂም ዲያዝ፣ ሳይባሪ እና ፓፔ ጉዬ በካፍ የወንዶች የ2026 የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች የመጨረሻ አምስት ውስጥ ተካትተዋል።
የባለፈው ዓመት አሸናፊ አሽራፍ ሃኪሚ፣ ሳዲዮ ማኔ፣ ብራሂም ዲያዝ፣ ኢስማኤል ሳይባሪ እና ፓፔ ጉዬ ለካፍ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋችነትን ለማሸነፍ የመጨረሻ ዕጩዎች ኾነዋል።
የካፍ የዓመቱ ተጫዋች አሸናፊ በፈረንጆቹ ታኅሣሥ 2 በናይጀሪያ ሌጎስ በሚካሄደው ሥነ ሥርዓት ይታወቃል።
አሽራፍ ሃኪሚ በክለቡ ፓሪስ ሴንት-ጀርመን እና ከሀገሩ ብሔራዊ ቡድን ጋር ድንቅ ጊዜን አሳልፏል።
በዓመቱ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ እና የፈረንሳይ ሊግ 1 ዋንጫን ከክለቡ ጋር አሳክቷል።
በሀገሩ ሴኔጋል እና በክለቡ አልናስር ጥሩ ጊዜን ያሳለፈው ሳዲዮ ማኔ ለአሸናፊነት የሚጠበቅ ሌላኛው ተጫዋቾች ነው።
በ2019 እና 2022 የካፍ የዓመቱ ምርጥ የተባለው ማኔ ለሦሥተኛ ጊዜ ለማሸነፍ የመጨረሻ እጩዎች ውስጥ ገብቷል።
ሞሮኳዊው የሪያል ማድሪድ አጥቂ ብራሂም ዲያዝ፣ ሴኔጋላዊው የቪላሪያል አማካይ ፓፔ ጉዬ፣ ሞሮኳዊው እስማኤል ሳይባሪ እና ሌሎችም እጩ ኾነው የቀረቡ ተጫዋቾች ናቸው።
በባዘዘው መኮንን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



