ሴኔጋል ከፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኾነች።

0
67

ዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (CAS) የካፍን ውሳኔ በመሻር የሴኔጋልን የ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊነት አጽድቋል።

በፍጻሜው ሴኔጋል አዘጋጇን ሞሮኮን በሜዳዋ ላይ ብታሸንፍም፤ በጨዋታው መካከል የዳኛን ውሳኔ ተቃውመው ወደ መልበሻ ክፍል በገቡ የሴኔጋል ተጫዋቾች ምክንያት ካፍ ዋንጫውን ለሞሮኮ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል።

የሴኔጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን የካፍን ውሳኔ በመቃወም ይግባኙን ለሎዛኑ ፍርድ ቤት ሲያቀርብ ቆይቷል።

ትናንት የስፔኑ ማርካ ጋዜጣ ፍርድ ቤቱ ቀድሞ ለሞሮኮ ወስኗል ሲል ዘግቦ በመገናኛ ብዙኀን ቢሰራጭም፤ ዛሬ ይፋ በኾነው መረጃ ሴኔጋል ሕጋዊ አሸናፊ መኾኗን አረጋግጣለች።

ዘጋቢ፦ ጥበቡ ሰለሞን

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_15_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here