አርሰናል ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ ተጠባቂው የሻምፒዮንስ ሊግ ፍልሚያ!

0
74

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዎኑ አርሰናል እና የጀርመኑ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ዛሬ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ 5ኛ ዙር ጨዋታ በኤምሬትስ ስታዲየም ይገናኛሉ።

የሚኬል አርቴታው አርሰናል በፕሪሚየር ሊጉ ከተከታዮቹ በስድስት ነጥብ ሲመራ፣ በሁሉም ውድድሮች 10 ተከታታይ ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ ላይ ይገኛል። በሻምፒዮንስ ሊጉም ከአራት ጨዋታዎች 10 ነጥብ ሠብሥቦ 3ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲኾን፣ ኤቤሬቺ ኤዜ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ቡድኑን እየመራ ነው።

በአንጻሩ የኒኮ ኮቫች ቡድን ቦሩሲያ ዶርትሙንድ በቡንደስሊጋው ሳይሸነፍ ቀዳሚ ሲኾን፣ በሻምፒዮንስ ሊጉ ደግሞ በ9 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። አጥቂው ሰርሁ ጊራሲ በውድድሩ አራት ግቦችን በማስቆጠር የዶርትሙንድ ዋነኛ የማጥቃት ስጋት ነው።

በአርሰናል በኩል ዴቪድ ራያ በትከሻ ጉዳት ምክንያት መሰለፉ አጠራጣሪ ሲኾን፣ ቡካዮ ሳካ እና ማርቲን ዙቢሜንዲ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጭ ናቸው።

በዶርትሙንድ በኩል ደግሞ ካርኒ ቹክዉሜካ እና ኤምሬ ቻን ጨምሮ በርካታ ተጫዋቾች በጉዳት አይሰለፉም።

በሻምፒዮንስ ሊግ ታሪክ ሁለቱ ቡድኖች ስምንት ጊዜ ተገናኝተው አርሰናል 4፣ ዶርትሙንድ 3 ድሎችን ሲያስመዘግቡ አንድ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል። የኦፕታ ሱፐር ኮምፒውተር ግምት ደግሞ ለአርሰናል የማሸነፍ ግምት 65 ነጥብ 2 በመቶ ሰጥቶታል። ጨዋታውም ምሽት 5፡00 ይካሄዳል።

በሌሎች ጨዋታዎች፦

👉ማንቸስተር ሲቲ ከናፖሊ

👉ሪያል ማድሪድ ከፒ.ኤስ.ቪ

👉ኮሞ ከኤ.ኢ.ኬ አቴንስ

👉ፌየኖርድ ከፖርቶ

👉አርቢ ላይፕዚግ ከሌንስ

👉ስሎቫን ብራቲስላቫ ከሪያል ቤቲስ በተመሳሳይ 5፡00 ጨዋታቸውን ሲያደርጉ

👉ቦዶ/ግሊምት ከላስክ እና

👉ጋላታሳራይ ከአስቶን ቪላ በተመሳሳይ ሰዓት 2፡45 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_15_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here