ትናንት በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የተካሄደውን የኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በስታዲየም ተገኝተው ከተከታተሉት ታላላቅ የመንግሥት መሪዎች መካከል የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አንዱ ናቸው።
በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው የዓለም ወጣቶች ኦሎምፒክ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ያደረጉ ውጤታማ አትሌቶችም በጨዋታው ታድመዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመስገን ጥሩነህም ለአትሌቶቹ ተከታዩን መልዕክትም አስተላልፈዋል።
“ታዳጊ አትሌቶቻችን የኢትዮጵያን የድል ጉዞ የምታድሱ ሀገራዊ ኩራቶቻችን ናችሁ!
በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው የ2026 የዓለም ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን በዓለም የአትሌቲክስ ሜዳሊያ ሰንጠረዥ በአንደኝነት እንድታጠናቅቅ ያስቻሉትን ታዳጊ አትሌቶቻችንን በአካል አግኝቼ አበረታትቻለሁ።
በአፍላ ዕድሜያችሁ በዓለም መድረክ ባሳያችሁት ብቃት እና ባስመዘገባችሁት ድል የሀገራችሁን ሰንደቅ በክብር ከፍ አድርጋችኋል።
ለመላው ኢትዮጵያውያን ደስታ እና ኩራት፣ ለታዳጊው ትውልድም ታላቅ ተስፋ እና ተምሳሌት ኾናችኋል።
የአሁኑ ድላችሁ ለነገ የላቀ ስኬት መነሻ እና መሠረት ነው። በራሳችሁ እመኑ፤ ህልማችሁን አሳድጉ፤ ከዛሬው ድል የበለጠ ከፍታን አልሙ።
ለመጪዎቹ የዓለም ሻምፒዮናዎች እና ኦሎምፒክ ጨዋታዎች በበለጠ ብቃት፣ በትጋት እና በቁርጠኝነት ተዘጋጁ።
መንግሥት በቀጣይ የስኬት ጉዟችሁ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል።
እናንተም ብቃት እና ችሎታችሁን በቀጣይነት እያዳበራችሁ፣ ህልማችሁን እያሳደጋችሁ የሀገራችሁን ስም እና ሰንደቅ በዓለም አደባባይ በተከታታይ ከፍ ለማድረግ በጽናት ለድል እንድትሰለፉ አደራ እላለሁ” የሚል መልዕክት ማስተላለፋቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገልጿል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_09_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



