የሞዛምቢክ ብሄራዊ ቡድን ባሕር ዳር ገባ።

0
43

በአፍሪካ ዋንጫ 4ኛ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ነገ የሚጫወተው የሞዛምቢክ ብሄራዊ ቡድን ባሕር ዳር ገብቷል።

41 ልዑካን የያዘው ብሄራዊ ቡድኑ ደጅአዝማች በላይ ዘለቀ አለም አቀፍ ኤርፖርት ዛሬ ከስዓት በኃላ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል።

ኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ የአፍሪካ ዋንጫ 4ኛ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ነገ 10፡00 በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስቴዲየም ያከናውናሉ።

ሁለቱ ብሄራዊ ቡድኖች ባሳለፍነው አርብ ባደረጉት ጨዋታ ዋልያዎቹ 1 ለ 0 ማሸነፋቸው አይዘነጋም።

‎

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_07_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here