በመጪው ማክሰኞ ኅዳር/8/2019 ዓ.ም ባሕር ዳር ከተማ ለሚካሄደው እና ለብሔራዊ ቡድናችን (ዋሊያዎቹ) እጅጉን ወሳኝ ለኾነው ጨዋታ ከቲኬት ጋር ተያይዞ ባለፈው ከሴኔጋል ጋር ጨዋታ የነበረውን የደጋፊዎች እንግልት እና መጉላላት ለመቅረፍ ሰፊ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ።
ስለኾነም ከዛሬ ሰኞ ኅዳር 7/2019 ዓ.ም 4:30 ጀምሮ ከዲጂታል ቲኬት ሽያጮች ጎን ለጎን የእጅ በእጅ ሽያጮችን በተመረጡ እና ከፍተኛ የሕዝብ ፍሰት ባሉባቸው የባሕር ዳር ከተማ ቦታዎች የወረቀት ቲኬቶችን መሸጥ ተጀምሯል።
የቲኬት መሸጫ ቦታዎችም፦
1. ፓፒረስ ማደያው ላይ
2. አዝዋ ሆቴል በር ላይ
3, ሙሉዓለም የባሕል መዕከል በር ላይ እየተካሄደ ነው የሚገኘው።
በቀጣይ አባይ ማዶ እና ገጠር መንገድ ላይ የቲኬት ሽያጩ ይቀጥላል ነው የተባለው።
ማሳሰቢያ ቲኬቱ QR ኮድ ስላለው ለሌላ ሰው አያሳዩ።
ትኬቶችን ባሉበት ኾነው ለመቁረጥ በ online የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ።
https://ethiopiaff.org/matches/XFBAC2D3
በጥበቡ ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



