በቅርቡ ከ23 ዓመታት በኋላ ከብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ራሱን ያገለለው ፖርቹጋላዊው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ፣ በፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አባላት ልዩ የምስጋና እና የሽኝት ዝግጅት እንደተዘጋጀለት ታውቋል።
ፖርቹጋል ዛሬ በኔሽንስ ሊግ ዴንማርክን በምትገጥምበት ጨዋታ ሁሉም የቡድኑ አባላት ለርሱ መታሰቢያነት 7 ቁጥር መለያ ለብሰው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ተዘግቧል።
ውሳኔው የተላለፈው የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ፔድሮ ፕሮዌንካ፣ አሰልጣኙ ሆርጌ ጄሱስ እንዲሁም የቡድኑ ተጫዋቾች ብሩኖ ፈርናንዴዝ፣ በርናንዶ ሲልቫ እና ሩበን ዲያዝ ካደረጉት ውይይት በኋላ ነው።
በጨዋታው ሰባተኛ ደቂቃ ላይ ደግሞ በስታዲዮ ሚዩኒሲፓል የታደሙ እግር ኳስ ተመልካቾች ከመቀመጫቸው ተነስተው ለሮናልዶ ልዩ ክብር እንደሚሰጡትም ተዘግቧል።
ከክሪስቲያኖ ሮናልዶ የሰባት ቁጥር ጋር የተያያዙ መታሰቢያዎች በተጨማሪ፣ በልምምድ ካምፕ ይጠቀምበት የነበረው ክፍልም በሌላ ተጫዋች እንዳይያዝ ተወስኗል።
ይህ የኔሽንስ ሊግ ጨዋታ ሮናልዶ ከዘጠኝ ቀናት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ስንብቱን ካወጀ በኋላ የሚደረግ ነው።
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን መጫወት ከጀመረ በኋላ ፖርቹጋል በታሪኳ ደርሳበት የማታውቀውን ስኬት ስታገኝ፤ በአራት ታላላቅ ውድድሮች ለፍፃሜ ደርሳ የአውሮፓ ዋንጫን ጨምሮ ሶስት ታላላቅ ዋንጫዎችን አንስታለች።
ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን በ234 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 146 ግቦችን ከመረብ ያሳረፈው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ፤ በዓለም እግር ኳስ ታሪክ በብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ከፍተኛውን ግብ ያስቆጠረ ቀዳሚው ተጫዋች ነው።
ምሽት 4:45 ከክሪስቲያኖ ሮናልዶ ስንብት በኋላ በበርናንዶ ሲልቫ አምበልነት ዴንማርክን የሚገጥምበት የስታዲዮ ሚዩኒሲፓል ዲ ብራጋ ጨዋታ፣ ፖርቹጋል የድኅረ ክሪስቲያኖ ሮናልዶን አዲስ ምዕራፍ የምትጀምርበት ይሆናል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_05_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



