የአለም አትሌቲክስ የአመቱን ምርጦች ይፋ ሲያደርግ ትዕግሥት አሰፋ አራተኛ ሆናለች።
በአመቱ ከተደረጉ ሰባት ሜጀር ማራቶን መካከል ሁለቱን በአስደናቂ ሁኔታ ለንደንና በርሊን ላይ ማሸነፍ የቻለችው ትዕግስት በተሰጣት ድምጽ መሰረት አራተኛ ሆናለች።
በሌላ በኩል ለ2026 የሴቶች የአለም ምርጥ ሽልማት የመጨረሻ ሶስት እጩዎችን የአለም አትሌቲክስ ይፋ ሲያደርግ ከአሜሪካ የ100ና 200 ሜትር ባለክብሯ ሜሊሳ ጀፈርሰን ውድስ እና የ110 ሜትር መሰናክል ኮከቧ ማሳይ ሩሴል ተካተዋል።
ስዊዘርላንዳዊቷ ኦድሬ ዎሮ ለሽልማቱ እጩ ሆነው ከተፋጠጡት መካከል ሆናለች።
ሽልማቱንም በመጪው የፈረንጆቹ ህዳር 29 በሞናኮ ይደረጋል ።
ሐናማርያም መስፍን
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ህዳር _02_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



