👉በዓለም አቀፉ የተጫዋቾች ማኅበር ይፋ በተደረገው የ2026 የዓመቱ ምርጥ ስብስብ ውስጥ የሚከተሉት ተጫዋቾች ተካተዋል፦
ግብ ጠባቂ፡ ዴቪድ ራያ
ተከላካዮች፡ አሽራፍ ሀኪሚ፣ ፖው ኩባርሲ፣ ኑኖ ሜንዴስ
አማካዮች፡ ሮድሪ፣ ጁድ ቤሊንግሃም፣ ቪቲኛ
አጥቂዎች፡ ሊዮኔል ሜሲ፣ ኤርሊንግ ሆላንድ፣ ኪሊያን ምባፔ እና ላሚን ያማል ኾነው ተመርጠዋል።
👉የእግር ኳስ ተጫዋቾች የ2025/26 የውድድር ዓመት ምርጥ ሦሥት ተከላካዮችን መርጠዋል። በዚህም መሠረት የፒኤስጂው የክንፍ ተከላካይ አሽራፍ ሀኪሚ በ40 ነጥብ 9 በመቶ ድምጽ የአንደኝነት ደረጃን ሲይዝ፣ የባርሴሎናው ወጣት ተከላካይ ፓው ኩባርሲ በ26 ነጥብ 8 በመቶ ሁለተኛ ደረጃን አግኝቷል። ሌላኛው የፒኤስጂ ተከላካይ ኑኖ ሜንደስ ደግሞ በ25 ነጥብ 5 በመቶ ድምጽ በሦሥተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
👉ዳቪድ ራያ በተጫዋቾች ድምጽ የ2025/26 ውድድር ዓመት ምርጥ ግብ ጠባቂ ተብሏል። የተጫዋቾች ማኅበር ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት የአርሰናሉ ግብ ጠባቂ ዳቪድ ራያ በ51 ነጥብ 9 በመቶ ከፍተኛ ድምጽ በማግኘት በአንደኝነት ሲቀመጥ ቲቦ ኮርቱዋ በ38 ነጥብ 6 በመቶ ሁለተኛ እና ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ በ32 ነጥብ 7 በመቶ ሦሥተኛ ደረጃ ተቀምጧል።
👉ፓው ኩባርሲ የ2026 የጎልደን ቦይ ሽልማትን አሸነፈ። የባርሴሎናው ወጣት ተከላካይ ፓው ኩባርሲ የ2026 የጎልደን ቦይ አሸናፊ በመኾን ሽልማቱን ያገኘ 6ኛው ስፔናዊ ተጫዋች ኾኗል። በዚህም ስፔን በታሪክ ብዙ የጎልደን ቦይ አሸናፊ ተጫዋቾችን ያፈራች ሀገር መኾን ችላለች። የስፔን የጎልደን ቦይ አሸናፊዎች በ2026፡ ፓው ኩባርሲ፤ በ2024 ላሚን ያማል፤ በ2022፡ ጋቪ፤ በ2021 ፔድሪ፤ በ2012 ኢስኮ እና 2006 ሴስክ ፋብሬጋስ ናቸው።
👉”ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፖርቱጋልን በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ከፍ ያለ ቦታ ላይ አስቀምጧል” ሲል ሮማሪዮ ተናገረ፡ብራዚላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሮማሪዮ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድን መሰናበቱን ተከትሎ ከፍተኛ አድናቆቱን ገልጿል።
ሮማሪዮ በሰጠው አስተያየት፡ “ከሮናልዶ መምጣት በፊት ፖርቹጋል ጥሩ ቡድን እንጂ ለትልልቅ ዋንጫዎች የምትፎካከር እና ተቃራኒዎችን የምታስፈራ አልነበረችም። በእርሱ መምጣት ግን ሁሉም ነገር ተቀይሯል፤ ፖርቹጋልን በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ላይ በማስቀመጥ የ2016 አውሮፓ ዋንጫን እና ሁለቱን የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ዋንጫዎች እንድታሸንፍ አድርጓል” ብሏል።
👉ላሚን ያማል በዓለም እግር ኳስ አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል። የባርሴሎና እና የስፔን ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ላሚን ያማል በታዳጊ ዕድሜው ሁለት ጊዜ በዓለም አቀፉ የተጫዋቾች ማኅበር የዓመቱ ምርጥ 11 ሥብሥብ ውስጥ በመካተት በታሪክ የመጀመሪያው ተጫዋች መኾን ችሏል።
👉ኦኔስት አሃኖር የጣሊያን የጎልደን ቦይ አሸናፊ ኾነ። ባለፈው የክረምት የዝውውር መስኮት ከአታላንታ በ50 ሚሊዮን ዩሮ ዋጋ ቼልሲን ተቀላቅሎ በአሁኑ ሰዓት በውሰት በክሪስታል ፓላስ የሚገኘው ወጣቱ ተከላካይ ኦኔስት አሃኖር የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች በመባል የጣሊያን ጎልደን ቦይ አሸናፊ ኾኗል። አሃኖር በቅርቡ በአሠልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ ለጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ጥሪ የተደረገለት ሲኾን በብሔራዊ ቡድኑ የወደፊት ዕቅድ ውስጥ ትልቅ ቦታ እንደተሰጠው ተገልጿል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ህዳር_01_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



