አጫጭር ስፖርታዊ መረጃዎች፦

0
106
ማይክል ካሪክ ከማንቸስተር ዩናይትድ አሠልጣኝነት በገዛ ፍቃዱ እንደማይለቅ ገለጸ። የማንቸስተር ዩናይትዱ አሠልጣኝ ማይክል ካሪክ ከአስቶን ቪላ ጋር 4 ለ 4 ከተለያየበት ጨዋታ በኋላ ስለ መጪው ዕድሉ ተጠይቆ በገዛ ፍቃዱ ሥራውን የመልቀቅ ምንም አይነት ሀሳብ እንደሌለው ተናግሯል። ካሪክ በሰጠው አስተያየት እንዳለው “በቂ ጨዋታዎችን አላሸነፍንም፣ ነገር ግን ሥራችንን ቀጥለን የምንሠራቸውን ስህተቶች በማስተካከል ጨዋታዎችን እንደምናሸንፍ እጠብቃለሁ” ብሏልካሪክ በውጤት ቀውስ ውስጥ ቢኾንም ክለቡን ለቆ የመውጣት ፍላጎት እንደሌለው እና ሥራውን መቀጠል እንደሚፈልግ አረጋግጧል። አሽሊ ያንግ በማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋቾች ላይ ጠንከር ያለ ትችት ሰነዘረ
የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች አሽሊ ያንግ የክለቡ ወቅታዊ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ እና የተጫዋቾች ትስስር አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን በመግለጽ ጠንከር ያለ ትችት አቀረበ። አሽሊ ያንግ በሰጠው አስተያየት በዩናይትድ ተጫዋቾች መካከል ያለው የመግባባት እና የሜዳ ላይ አመራርነት እጥረት ለቡድኑ ደካማ እንቅስቃሴ ዋነኛ ምክንያት መኾኑን ጠቁሟል። “አንዳንድ ጊዜ የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋቾች እርስ በርሳቸው እንኳን የሚተዋወቁ አይመስሉም። የቡድኑን ጨዋታ መመልከት በጣም ከባድ ኾኗል። ተጫዋቾች ከዚህ የተሻለ የላቀ ኀላፊነት እና ቁርጠኝነት ሊያሳዩ ይገባል” ብሏል። ያንግ አክሎም በቡድኑ ውስጥ በርካታ ወጣት ተጫዋቾች ቢኖሩም፣ በከባድ አጋጣሚዎች ላይ ኀላፊነት ወስደው ቡድኑን የሚመሩ ጠንካራ መሪዎች በሜዳ ላይ መኖራቸው አስፈላጊ መኾኑን አስገንዝቧል። ዶሚኒክ ሶቦስላይ በአስተማማኝነት ጤነኛ ባይኾንም ለሃንጋሪ ብሔራዊ ቡድን ለመጫወት ይፈልጋል ሲሉ አሠልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ ገለጹ። የሊቨርፑሉ አማካይ ዶሚኒክ ሶቦስላይ ከጉልበት ጉዳት ጋር ተያይዞ ሙሉ በሙሉ ለጨዋታ ብቁ እንዳልኾነ አሠልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ ገልጸዋል። ቢኾንም ግን ተጫዋቹ ለሃንጋሪ ብሔራዊ ቡድን ባለው ከፍተኛ ፍቅር ምክንያት ለብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታ ለመድረስ የሚችለውን ሁሉ እንደሚያደርግ አሠልጣኙ ተናግረዋል። አሠልጣኙ ይህን ይበሉ እንጅ የሊቨርፑል የሕክምና ባለሙያዎች የተጫዋቹን የአካል ብቃት ሁኔታ ገምግመው ከሃንጋሪ ብሔራዊ ቡድን ጋር መጓዝ ይችል እንደኾነ ውሳኔ የሚሰጡ ይኾናል ነው የተባለው። ክሪስታል ፓላስ አሠልጣኝ ፒየር ሴጅን ሊያሰናብት ነው። ክሪስታል ፓላስ ፈረንሳዊውን አሠልጣኝ ፒየር ሴጅን ከኀላፊነታቸው ለማሰናበት መወሰኑ ተረጋግጧል። ዘ አትሌቲክ እንደዘገበው ከኾነ ክለቡ በውድድር ዓመቱ ባሳየው ደካማ አጀማመር ምክንያት ከአሠልጣኙ ጋር ለመለያየት ወስኗል።አሠልጣኙን ለማሰናበት ምክንያት የኾነው ቡድኑ በሊቨርፑል 3 ለ 1 መሸነፉን ተከትሎ  በፕሪሚየር ሊጉ የሰንጠረዥ ግርጌ ላይ መቀመጡ ነው። አሠልጣኙ በክለቡ ቆይታቸው ካደረጓቸው 16 አጠቃላይ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት 5 ጨዋታዎችን ብቻ ሲኾን፣ በሊጉ ካደረጓቸው 10 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት 2ቱን ብቻ ነው። ለክሪስታል ፓላስ ይሾማሉ ተብለው ከተያዙ ዕጩ አሠልጣኞች መካከልም ቶማስ ፍራንክ፣ ሻን ዳይች እና ግራሃም ፖተር ይገኙበታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here