ኩሪኝ ደስታ በ400 ሜትርና ሲፈን ታዬ በቴኳንዶ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ አልቻሉም።

0
81
በ2 ምድብ 14 አትሌቶች በተሳተፉበት የሴቶች 400 ሜትር ግማሽ ፍጻሜ ኢትዮጵያ በኩሪኝ ደስታ ተወክላለች፡፡ በምድብ አንድ 5ተኛ ደረጃን ይዛ የጨረሰችው ኩሪኝ ወደ ፍጻሜው ማለፍ አልቻለችም፡፡ ከየምድቡ እስከ 4ኛ ያጠናቀቁና የተሻለ ሰአት ያላቸው ሁለት አትሌቶች ወደ
ቀጣዩ ተሻግረዋል። አትሌቷ ያስመዘገበችው 57 ሰከንድ ከ45 ማይክሮ ሰከንድ ለማለፍ አላስቻላትም፡፡ በዚህ 400 ሜትር ፍፃሜ አፍሪካ በሩዋንዳና ናይጀሪያ ትወከላለች፡፡ በሌላ በኩል ኢትዮጵያን በቴኳንዶ ስፖርት የወከለው ታዳጊው ሲፈን ታዬም አልተሳካለትም፡፡በውድድሩ
የመጀመሪያ ቀን ትላንት ከ48 ኪሎግራም በታች ሩብ ፍጻሜ ከሞልዶቫው ዲሚትሪ ባላጉላ ጋር ተጫውቷል፡፡ በጨዋታውንም 2 ለ ባዶ በሆነ ድምር ውጤት ተሸንፎ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ሳያልፍ ቀርቷል፡፡ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎችም ትላንት ሲደረጉ ለፍጻሜ ያለፉት ግብጽና ፈረንሳይ
ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡ ግብጽም በተወዳዳሪዋ አማካኝነት ፈረንሳይን 2 ለባዶ በማሸነፍ ከ48 ኪሎግራም በታች የወርቅ ሜዳልያውን ወስዳለች፡፡
ሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here