ከተጀመረ ቀናትን ያስቆጠረው የዳካር ወጣቶች ኦሎምፒክ በአትሌቲክስ ውድድሮቹ ተመልሷል።

0
29
በመምና በሜዳ ተግባራት ውድድሮቹ ሲደረጉ የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ቡድንም በሁለት የፍጻሜና የማጣሪያ ውድድሮች ፉክክሩን ይጀምራል።
በሴቶች 2000 ሜትር መሰናክል ፍጻሜ አትሌት ጻድቃን መኮንን ምሽት 12 ከ20 ላይ ትወዳደራለች። የኢትዮጵያን የመጀመሪያ ሜዳልያ ለማምጣት የምትገባው ጻድቃን ከዩጋንዳዋ ራቼል ቸሊሞና ከኬንያዋ አቢጌል ኮስጊ ከፍተኛ ፉክክር ይጠብቃታል።
ባጠቃላይም 11 አትሌቶች በፍጻሜው ይፎካከራሉ።
ቀጥሎ በሚደረገው ውድድር የወንዶች 3000 ሜትር ፍጻሜ ነው። አትሌት ጎይቶም መኮንን ኢትዮጵያን ወክሎ ይሮጣል።
ከነዚህ የፍጻሜ ውድድሮች ቀደም ብሎ 11 ሰአት ከ25 በሚደረግ የሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ አትሌት ነፃነት ሰለሞን ትወዳደራለች።
2 ደቂቃ ከ04 ሰከንድ ከ72 ማይክሮ ሰከንድ የራሷ ፈጣን ሰአት ያላት ነጻነት ወደ ፍጻሜው እንደምታልፍም ቅድመ ግምት ተሰጥቷታል።
እንዲሁም በሴቶች 400 ሜትር አትሌት ቁርኝ ደስታ ምሽት 1 ሰአት ከ20 ላይ የማጣሪያ ፉክክሯን ታካሂዳለች።
ሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here