በሁለተኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ በሜዳው ባህርዳር አለም አቀፍ ስቴድየም ሲዳማ ቡናን ገጥመው አንድ ለባዶ በማሸነፍ የውድድር አመቱን የመጀመሪያ ድል ያገኙት የጊዮን ንግስቶቹ ዛሬ ተከታታይ ድል ለማስመዝገብ ወደ አሰላ አቅንተዋል።
የባህርዳር ከነማ ሴቶች ዛሬ 9 ሰአት ባለፈው አዲስ አበባ ላይ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ከተሸነፉት ጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማእከል ሴቶች ጋር ይጫዎታሉ።
ባለሜዳ የሆኑት ጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማእከል ከሽንፈት ለመውጣት ባህርዳር ለተከታታይ አሸናፊነት ፉክክራቸውን ያደርጋሉ።
10 ሰዓት ላይ ያለፈው የውድድር አመት ጠንካራ ተፎካካሪ የነበሩት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚያከናውኑት ጨዋታ ይጠበቃል።
ንግድ ባንክ የሊጉ መሪ ሲሆን ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምስተኛ ላይ ሆኖ ነው የሚጫወቱት።
በሌሎች መርሐ ግብሮች መቻል ከድሬዳዋ ከተማ 8:00 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ሀዋሳ ከተማ ከቦሌ ክፍለ ከተማ 10 ሰዓት ላይ በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
አዳማ ከተማ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ በወንጂ ስታዲየም 9 ሰአት ይጫዎታሉ።
በዳናይት ሲሳይ
አሚኮ #ስፖርት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



