በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 10 ሳምንት ጨዋታ ዛሬም ሲቀጥል ማንቸስተር ዩናይትድ እና የአስቶን ቪላን የሚያገናኘው ጨዋታ ተጠባቂ ኾኗል።
ማንቸስተር ዩናይትድ ዛሬ ምሽት 1፡30 በኦልድ ትራፎርድ አስቶንቪላን ያስተናግዳል።
የማንቸስተር ዩናይትድ ወቅታዊ አቋም፦
በሊጉ ከሰባት ጨዋታዎች ወዲህ ድል አላስመዘገበም፤ በደረጃ ሰንጠረዡም 18ኛ ላይ ተቀምጧል።
በሻምፒዮንስ ሊጉ ሮማን 3 ለ 2 ካሸነፈበት ድል በመነሳት አሁን ላይ አሸናፊነቱን ለማስቀጠል ወደ ሜዳ ይገባል።
በሊጉ እስካሁን 15 ግቦች የተቆጠሩበት ሲኾን እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን ከ1972/73 የውድድር ዓመት ወዲህ በመጀመሪያዎቹ 9 የሊግ ጨዋታዎች አንድ ድል ብቻ ያስመዘገበው ክለቡ ዛሬ ማሸነፍ ይጠበቅበታል።
የአስቶን ቪላ ወቅታዊ አቋም፦
በሊጉ ያደረጋቸውን ያለፉት አምስት ጨዋታዎች አልተረታም።
አሠልጣኝ ኡናይ ኤምሪ ለአስቶን ቪላ 200ኛ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ኒኮላስ ጃክሰን በስምንት የሊግ ጨዋታዎች አምስት ግቦችን በማስቆጠር የፊት መስመር ቁልፍ ተጫዋች ነው።
የእርስ በእርስ ግንኙነታቸው፦
ማንቸስተር ዩናይትድ ከቪላ ጋር በኦልድ ትራፎርድ ካደረጓቸው 31 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች 24ቱን አሸንፏል። ቪላ ማሸነፍ የቻለው በሁለቱ ብቻ ነው።
ኡናይ ኤምሪ አስቶን ቪላን ከተረከቡ ወዲህ ወደ ኦልድ ትራፎርድ ተጉዘው ባደረጓቸው አምስት ጨዋታዎች አላሸነፉም።
የተጫዋቾች ጉዳት እና ቅጣት፦
በማንቸስተር ዩናይትድ በኩል ካርሎስ ባሌባ፣ ማርከስ ራሽፎርድ፣ ቤንጃሚን ሼሽኮ፣ ሉክ ሾው እና ማኑኤል ኡጋርቴ በጉዳት፤ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በቅጣት ከጨዋታው ውጪ ናቸው።
በአስቶን ቪላ በኩል ደግሞ ማቲ ካሽ በቅጣት፣ አማዱ ኦናና በጉዳት አይሰለፉም።
ሌሎች ጨዋታዎችም ሲደረጉ ዛሬ 11፡00 ክሪስታል ፓላስ ከሊቨርፑል፣ ብራይተን ከብሬንትፎርድ፣ ኢፕስዊች ከቦርንማውዝ፣ እንዲሁም ሰንደርላንድ ከቼልሲ ጨዋታዎቻቸውን ያደርጋሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



