የዩናይትድ ኃላፊዎች ዛሬ ባደረጉት ስብሰባ ካሪክ የመፍትሄ መፈለጊያ ቀጣይ ጨዋታዎች እድል ተሰጥቶታል።
የ45 ዓመቱ አሰልጣኝ የቅዳሜውን የማንቸስተር ዩናይትድና ቼልሲን ጨዋታ ጨምሮ ማንችስተር ዪናይትድን ሲመራ እንዲቆይ ተጨማሪ ጊዜ ተሰቶታል።
ማንቸስተር ዩናይትድ በሁሉም ውድድሮች ባለፉት 8 ተከታታይ ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም።
በተለይ በቦርንማውዝ 3ለ0 ከተሸነፉ በኋላ የአሰልጣኙ ቆይታ ጥያቄ ውስጥ ገብቶ ነበር።
አሰልጣኝ ዩልያን ኔግልስማን ወይም ኤዲ ሀው ካሪክን ሊተኩ እንደሚችሉ ቢወራም አሰልጣኙ ግን በዩናይትድ እንዲቆይ በክለቡ አመራሮች ስምምነት ተደርሷል
መለሰ ግዛቸው
#FootballNews
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_17_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



