ወላይታ ዲቻ የሚቀጥሉትን 10 ጨዋታዎች በዋና አሰልጣኙ አይመራም፡፡

0
109

 

የኢትዮጰያ ፕሪሚር ሊግ 3ተኛ ሳምንት ረቡዕ እለት በተደረጉ ጨዋታዎች መጠናቀቁን ተከትሎ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተላልፈዋል፡፡

ወላይታ ዲቻ በባህርዳር ከተማ 3 ለ 1 ከተሸነፈ በኋላ ያልተገባ ባህሪ ያሳዩት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የ10 ጨዋታዎች ቅጣት ተላልፎባቸዋል፡፡

በመርሃግብሩ መጠናቀቂያ ጭማሪ ደቂቃዎች ላይ 90+4ኛው በተፈጠሩ አለመግባባቶች የወላይታ ድቻው አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳደብ እና በቀይ ካርድ ከሜዳ በመውጣት ለፈጸሙት ጥፋት 6 ጨዋታዎች ተቀጥተዋል፡፡

እንዲሁም ከቀይ ካርዱ ውሳኔ በኋላ ከ4ተኛ ዳኛው ጋር ለፀብ በመጋበዛቸው እና ጨዋታውን ለ3 ደቂቃዎች በማዘግየታቸው 4 ጨዋታዎች ዳግም እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል፡፡

በተጨማሪም 10ሺህ ብር እንዲከፍሉ የውድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ መወሰኑን አሳውቋል፡፡

የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች የጨዋታውን ሁለተኛ ረዳት ዳኛ በድንጋይ በመወርወር መምታታቸውን የሚገልጽ ሪፖርት የቀረበባቸው በመሆኑ የ50ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎባቸዋል።

በዚሁ ጨዋታ ድል ያደረገው ባህርዳር ከተማ ከዳኞች አስቀድሞ ያልተመዘገቡ ተጫዋቾች ወደ መልበሻ ቤት ገብተዋል በሚል ሪፖርት የቀረበበት ሲሆን ለዚህ የክለቡ ጥፋትም 25 ሺህ ብር ቅጣት ተወስኖባቸዋል።

የኢትዮጰያ ቡናው ድልአዲስ ገብሬ በነገሌ አርሲ 3 ለባዶ በተረቱበት ጨዋታ ቀይ ካርድ ማየቱን ተከትሎ 3 ጨዋታ ቅጣት እንዲሁም 3 ሺህ ብር እንዲከፍል ወመሰኑን ሊግ አክሲዮን ማህበሩ ያወጣው መግለጫ ያሳያል፡፡

ሐናማርያም መስፍን
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_13_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here