አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ከበርሊን ማራቶን ከወጣ ከሶስት ሳምንት በኋላ በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ በቫሌንሺያ ግማሽ ማራቶን ሊሳተፍ መሆኑን ዘ ማራቶን ሃንድ ቡክ አስነበበ፡፡
ቀነኒሳ ከጉዳት በኋላ ወደ ውድድር ላይመለስ እንደሚችል ቢታሰብም የ44 ዓመቱ አትሌት ባልተጠበቀ መልኩ በፍጥነት ወደ ዉድድር ይፉ ሆኗል።
በዓለም ታዋቂ ከሆኑ የግማሽ ማራቶን ውድድሮች አንዱ የሆነዉ የቫሌንሲያ ላይ ቀነኒሳ ይሳተፋል፡፡
1 ሰዓት ከ22 ሰከንድ ቀነኒሳ በቀለ በግማሽ ማራቶን ከስድስት ዓመት በፊት የገባበት የግል ምርጥ ሰዓቱ ነው፡፡
የውድድሩ አዘጋጆች ደግሞ ዘንድሮ ግማሽ ማራኑ ከ59 ደቂቃ በታች እንዲጠናቀቅ ዕየሰሩ መሆኑ ታውቋል፡፡
44ኛ ዓመቱ ላይ የሚገኝው ቀነኒሳ ከጉዳቱ አገግሞ በሚያደርገው ውድድር ከወጣት አትሌቶች ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል።
ከተሳታፊ ኢትዮጱያያን መካከል ጀማል ይመር፣ ታደሰ ወርቁ እና መልክነህ አዘዘ ይገኙበታል፡፡
ቀነኒሳ በቀለ ከኢሉይድ ኪፕቾጌ ጋር በ2025 በኒዮርክ ከሮጠ በኋላ የመጀመሪያ የ2026 ፈረንጆች አመት ፉክክሩ ነው፡፡
በመለሰ ግዛቸው



