ለሚ ብርሃኑ እና ቡዜ ድሪባ በአምስተርዳም ማራቶንን አሸነፉ

0
113
በኔዘርላንድስ በተካሄደው የአምስተርዳም ማራቶን፤ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ባለ ድል ሆነዋል።
​በወንዶች ለሚ ብርሃኑ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ33 ሰከንድ በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆኗል።
የ31 ዓመቱ ለሚ የግል ምርጥ ሰዓቱን በአንድ ደቂቃ ያሻሻለ ሲሆን፤ የቦታውን ክብረወሰን ለመስበር ሦስት ሴኮንዶች ብቻ ቀርተውት ነበር።
​በሴቶች ውድድርም ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ቡዜ ድሪባ በ2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ10 ሴኮንድ በመግባት የቦታውን አዲስ ክብረወሰን በማስመዝገብ ጭምር አሸንፋለች።
ቡዜ ያለምዘርፍ የኋላው ይዛው የነበረውን የቦታውን ክብረወሰን የሰበረች ሲሆን፤ የግል ምርጥ ሰዓቷንም ከሦስት ደቂቃ በላይ አሻሽላለች።
ከውጭ
የቼልሲው ግብ ጠባቂ ኢሚላኖ ማርቲኔዝ ጉዳት ገጥሞታል።
ቡድኑ ትናንት ኤቨርተንን 2ለ0 በረታበት ጨዋታ የኤቨርተኑ ተከላካይ ብራንዝዌት እና ማርቲኔዝ ተጋጭተዋል።
በዚህም ማርቲኔዝ በገጠመው ጉዳት ቀዶ ጥገና አድርጓል። በዚህም ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል። ቢቢሲ እንዳስነበበው

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here