የሲዳማ ቡና የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ በድሬዳዋ ያካሄዳል።

0
88
በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ወክሎ በመወዳደር ላይ የሚገኘው ሲዳማ ቡና የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም በድሬዳዋ ስታዲየም ከሱዳኑ አልሂላል ኦምዱርማን ጋር ያደርጋል።
በመጀመሪያው ዙር የቻዱን ኤግሎንስ በደርሶ መልስ ጨዋታ በብቃት አሸንፎ ወደዚህ ዙር የተቀላቀለው የአሠልጣኝ ያሬድ ገመቹ ሥብሥብ ላለፉት አራት ቀናት በድሬዳዋ ያደረገውን ዝግጅት አጠናቅቆ ለዛሬው ጨዋታ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ኾኗል።
ከጉዳት ጋር በተገናኘ ለዛሬው ወሳኝ ጨዋታ የሲዳማ ቡና አምበል ያሬድ ባዬ በጉዳት ምክንያት ከሥብሥቡ ውጪ መኾኑ ተረጋግጧል።
ሁለገቡ የአማካይ እና የመስመር ተጫዋች ቢኒያም በላይም እንዲሁ በጨዋታው ላይ አይሰለፍም።
የመስመር አጥቂው መስፍን ታፈሰ ከቡድኑ ጋር ወደ ድሬዳዋ ያመራ ቢኾንም በጉዳት ምክንያት በጨዋታው መሰለፉ አጠራጣሪ ኾኗል።
ጨዋታውም ዛሬ ከቀኑ 10:00 በድሬዳዋ ስታዲየም የሚከናወን ይሆናል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here