ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ በቀጥታ ለማለፍ ከዩጋንዳ ጋር ያደረገችው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ አልተሳካም።

0
146

 

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከ ዩጋንዳ ጋር ወሳኝ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ አድርጋለች።

በሴካፋ ዞን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ግማሽ ፍፃሜ የደረሰው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከዩጋንዳ ጋር በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ በቀጥታ ለማለፍ ባደረገው ጨዋታ 4ለ0 ተሸንፏል።

ሁለቱ ሀገራት በምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ተገናኝተው 1 ለ 1 ተለያይተው የነበረ ቢኾንም ይህኛውን ጨዋታ ግን ዩጋንዳ አሸንፋ ወጥታለች።

የዩጋንዳን ግቦች ጁንየር ኦፎሮዝ፤ አርኖልድ ካዬምባ እና ሁለቱን ደግሞ ዩሱፍ ሴንዮንጋ አስቆጥረዋል

ኢትዮጵያ ለ3ኛ ደረጃ እንዲሁም ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የምታደርገው ጨዋታ በመጭው ሰኞ ይካሄዳል።

#FootballNews

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_07_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here