በፍቅር ማዕበል ውስጥ ኾኖ የተቋጨው የሜሲ እና አርጀንቲና ስንብት።

0
23
ሊዮኔል አንድሪያስ ሜሲ ለሰማያዊ እና ነጭ ማልያው የነበረው ፍቅር ረጅም ዓመታትን በዕንባ፣ በተስፋ መቁረጥ እና በትግል ውስጥ ያለፈ ነበር።
በመጨረሻም በትዕግስቱ ፍሬ በዓለም ዋንጫ ድል ደምቆ እና በታላቅነት ማማ ላይ ኾኖ ተሰናብቷል።
ኮከቡ ለሀገሩ ያበረከተው ውለታ ዋንጫዎችን ብቻ አልነበረም፣ ይልቁንም ለሚሊዮኖቹ ሕጻናት የማይበገር መንፈስን፣ ተስፋን እና ህልምን ያሰረጸ እንጂ።
ሜሲ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ያደረገው ጉዞ በሽንፈት አልቆ የተረሳ ታሪክ ሳይኾን በጽናት አልፎ የዓለምን ዘውድ በመድፋት ለዘላለም በታሪክ ሰነድ እና በእግር ኳስ አፍቃሪው ልብ ውስጥ ተቀርጾ የሚኖር የአሸናፊነት ተአምር ነው።
በኳስ ጥበቡ እልፎችን የማረከ በሜዳ ላይ አስደናቂ ተአምራትን ያሳየው ንጉሥ የሀገሩን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጎ በማውለብለብ የተሰናበተበት መንገድ በእውነትም ድንቅ እና ልብ የሚነካ ነው።
ኮከቦቻቸውን ማክበር እና ማላቅ የሚችሉበት አርጀንቲናውያን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ሜዳ ላይ ደስታን ለሰጣቸው የዘመኑ ንጉስ የሚገባውን ሽኝት አድርገውለታል።
የሊዮኔል ሜሲ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ስንብት በወርቃማ ቀለም የተጻፈ እና በዓለም እግር ኳስ ላይ የእንባ እና የደስታ ጠብታዎች በአንድ ላይ ያስመለከተ ልዩ የፍቅር እና የክብር ታሪክ ኾኖ ተቋጭቷል።
በታደሠ ሙላት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here