የባሎንዶር አዘጋጆች እንደገለጹት፣ አንድ ተጫዋች በአንድ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ከአንድ በላይ ሽልማቶችን እንዳያሸንፍ የሚከለክል ምንም ዓይነት ደንብ የለም ይላሉ ለኤስ ፒኤን በሰጡት መረጃ።
በዚህ መሠረት በወንዶች ዘርፍ ይህንን ታሪካዊ ዕድል የሚያገኙት ሁለቱ የስፔን እና የባርሴሎና ኮከቦች ላሚን ያማል እና ፓው ኩባርሲ ብቻ ናቸው። ሁለቱም ተጫዋቾች ለዋናው የባሎንዶር እና ለዓመቱ ኮከብ ወጣት ተጫዋች ኮፓ ትሮፊ ሽልማቶች በዕጩነት ቀርበዋል።
ፓው ኩባርሲ በዓለም ዋንጫ የኮከብ ወጣት ተጫዋች ሽልማትን ማሸነፉ የሚታወስ ሲኾን፣ ሁለቱንም ሽልማቶች በአንድ ምሽት በጥምረት የመውሰድ ፉክክሩን ከፍተኛ ግምት ካገኘው ላሚን ያማል ጋር እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ይህ ክስተት በባሎንዶር የረጅም ጊዜ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ሲኾን፣ ተጫዋቾቹ ይህንን ማሳካት የሚችሉ ከኾነ በዓለም እግር ኳስ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ይኾናል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



