የቤልጂየሙ እና የማንቸስተር ሲቲው አማካኝ ኬቪን ዲብሮይን ቡድኑ ቱርክን 3 ለ 0 በረታበት የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ጨዋታ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል።
በዚህም በዘመኑ የኔሽንስ ሊግ ባደረጋቸው የመጀመሪያ ሦሥት ጨዋታዎች በ3 ግቦች ላይ በቀጥታ ተሳታፊ መኾን ችሏል። ካለፈው አስቸጋሪ የውድድር ዘመን በኋላ ዲብሮይን ወደ ቀደመው ከፍተኛ ብቃቱ ለመመለስ በጥሩ አቋም ላይ ይገኛል።
በዓለም እግር ኳስ ውስጥ ከሚገኙ ተጽዕኖ ፈጣሪ አማካኞች ውስጥም አንዱ ነው።
ተጫዋቹ በድንቅ የኳስ እይታው፣ በሚገርም የኳስ ማሳለፍ አቅሙ እና በአርቆ ኳስን ለጓደኛ በማድረስ ብቃቱም ይታወቃል።
ለማንቸስተር ሲቲ በርካታ የፕሪሜር ሊግ እና የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን በማስገኘት ትልቅ ታሪክ ያለው ተጫዋችም ነው።
በርካታ ግቦችን በማመቻቸቱ “የአሲስት ንጉሥ” በሚል ቅጽል ስምም ይወደሳል። ይህ ጠንካራ ተጫዋች ታዲያ ወደ ቀደመ አቋሙ መመለሱን በአውሮፖ መድረክ ላይ እያሳየ ነው የሚገኘው።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_23_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



