አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የዮጋንዳ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ኾነው ተሾሙ

0
25
በተለያዩ የዕድሜ እርከኖች የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድኖችን በማሠልጠን የሚታወቁት አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የዮጋንዳ ሴቶች
ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ኾነው ተሾመዋል።
አሠልጣኙ እስከ 2029 ድረስ የሚያቆያቸውን ውል መፈረማቸው ተገልጿል።
ከሁለት ዓመታት በፊት ወደ ዮጋንዳ በመጓዝ የካምፓላ ኩዊንስ ክለብን ማሠልጠን የጀመሩት አሠልጣኝ ፍሬው፣ በቆይታቸው የሀገሪቱን የሊግ እና የፉፋ (FUFA) ዋንጫ ማሸነፍ ችለዋል።
ከክለቡ ጋር የነበራቸው ውል መጠናቀቁን ተከትሎም ከሳምንታት በፊት ከካምፓላ ኩዊንስ ጋር መለያየታቸው ይታወሳል።
በዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here