የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሴኔጋል አቻው ጋር በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ነገ መሥከረም 19/2019 ዓ.ም ጨዋታውን ያደርጋል።
ጨዋታውን በተመለከተ የቡድኑ ተጨዋቾች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የቡድኑ ተጫዋች ከነአን ማርክነህ ከዚህ ሜዳ ላይ የተጫወትነው ከአምስት ዓመታት በፊት ነው ብሏል።
“በባሕር ዳር ስታዲየም የሽንፈት ታሪክ የለንም፤ የነገውን ጨዋታም በተለመደው የአሸናፊነት መንፈስ እንጫወታለን” ብሏል።
ሌላኛው ተጨዋች አቡበከር ኑራ የነገው ጨዋታ ለእኛ ወሳኝ ጨዋታ ነው፤ ባለፈው በሱዳን ብሔራዊ ቡድን ያጣነውን ውጤት በነገው ጨዋታ ነጥብ ለማምጣት እንጫወታለን፣ የተሻለ ነገርም እንጠብቃለን ነው ያለው። ለዚህም የተሻለ ዝግጅት አድርገናል ብሏል።
የባሕር ዳር ሕዝብ ኳስ ወዳድ ነው፣ ከዚህ በፊት እንደሚሰጡት ድጋፍ ሁሉ በነገው ጨዋታም ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ እንጠብቃለን ብለዋል ተጫዋቾቹ።
#አሚኮ #Sport #Ethiopia🇪🇹 #CAF
#ባሕር_ዳር #መስከረም_18_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



