ለ6 ወራት ከሩጫው አለም የምትርቀው ትእግስት አሰፋ

0
97

 

በትላንትናው እለት ተጠባቂ ከነበሩት ሁነቶች መካከል 52ተኛው የበርሊን ማራቶን አንደኛውና ቀዳሚው ነው፡፡

በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አሸናፊ ኹነውበታል፡፡

በሴቶች ትእግስት አሰፋ በወንዶች ደግሞ ጉየ አዶላ ክብሩን ወስደዋል፡፡

ለ3ኛ ጊዜ ለማሸነፍና ክብረወሰን ለመስበር በልበ ሙሉነት በርሊን የደረሰችው ትእግስት አሰፋ ግን በመጨረሻ ሁለት ኪሎሜትሮች ያጋጠማት ጉዳት ለ6 ወራት ከሜዳ ሊያርቃት እንደሚችል ተነግሯል፡፡

የ2 ጊዜ የበርሊን ባለድልና የሴቶች ብቻ የአለም ክብረወሰን ባለቤቷ ትዕግሥት በ2026 የበርሊን ማራቶን አብዛኛውን የርቀቱን ኪሎሜትሮች የዓለም ክብረ ወሰን ለማሻሻል በሚያስችላት ፍጥነት መሮጥ ችላለች፡፡

ነገር ግን ከ40ኛው ኪሎሜትር በኃላ የተረከዝ ጅማቷ ላይ በደረሰባት ጉዳት ፍጥነቷ ሊቀንስ ችላል፡፡

አትሌቷ በከፍተኛ ሕመም ውስጥ ሆና በጽናትና በትእግስት በመቀጠል በ2 ሰአት 11 ደቂቃ ከ04 ሰከንድ በቀዳሚነት ለማጠናቀቅ ችላለች።

ይህ ሰአትም በሴቶች ማራቶን ታሪክ 3ተኛው ፈጣን ሰአት ሲሆን ለራሷም የግል ምርጥ ሰአት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ይህ የተረከዝ ጅማት ጉዳቱ ቀዶ ጥገና የሚያስፈልገው ሲሆን በዛሬው እለትም ይሄ እንደሚከናወን የአትሌቷ ማናጀር ጂያኒ ዲማዶና አሳውቋል፡፡ ይህ ጉዳትም እሰከ 6 ወር ድረስ ለማገገም ሊወስድባት ይችላል፡፡
ሐናማርያም መስፍን

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_18_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here