ባሕር ዳር ታላቁን አሕጉራዊ ጨዋታ ለማስተናገድ እና እንግዶቿን ለመቀበል ሙሉ ዝግጅቷን አጠናቅቃለች።
ውቢቷ ባሕር ዳር ከተማ የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በኢትዮጵያ እና በሴኔጋል ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የሚደረገውን ታላቅ የምድብ ጨዋታ ለማስተናገድ ሙሉ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው አስታውቀዋል።
የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስቴዲየም ከአምስት ዓመታት በኋላ እንዲህ ዓይነቱን ታላቅ አህጉራዊ ሁነት በብቃት ለማስተናገድ ዝግጁ መኾኑን የገለጹት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የስፖርት ቤተሰቦች እና የቱሪዝም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ወደ ከተማዋ ለሚመጡ እንግዶች የተለመደውን የላቀ እንግዳ ተቀባይነት በማሳየት የባሕር ዳር አምባሳደር እንዲኾኑ ጥሪ አቅርበዋል።
በመኾኑም መላው የስፖርት አፍቃሪ ማክሰኞ መስከረም 19/2019 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስቴዲየም በመገኘት የሀገራችን ብሔራዊ ቡድን ዋሊያዎቹን በሙሉ ወኔ እንዲደግፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
#አሚኮ #ለአሕጉራዊ_ጨዋታ_የባሕርዳር_ዝግጂት #ኢትዮጵያ
#ባሕር_ዳር #መስከረም_16_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



