የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከሱዳን ጋር ይጫወታል።

0
80

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን (ዋልያዎቹ) በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ከሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል።

ጨዋታው በደቡብ ሱዳን ጁባ ናሽናል ስታዲየም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ሲኾን ብሔራዊ ቡድኑ የማጣሪያ ጉዞውን በስኬት ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቅቋል።

በዚህ የሜዳ ውጭ ጨዋታ ዋልያዎቹ ሦሥት ነጥብ ይዘው በመውጣት ለቀጣዩ ጉዟቸው አዎንታዊ የሥነ-ልቦና የበላይነት ይይዛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ድል ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን። 🇪🇹⚽️

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_15_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here