ላሚን ያማል የሰጠው አስተያየት የስፖርት ቤተሰቡን እያነጋገረ ነው።

0
196

 

ላሚን ያማል “ሪያል ማድሪድ እንዲሸነፍ እየተመኘሁ ነው ጨዋታቸውን የምከታተለው” ብሏል።

የባርሴሎናው ወጣት ኮከብ ላሚን ያማል ከሞቪስታር ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ስለ ተቀናቃኞቹ የሰጠው ግልጽ አስተያየት የእግር ኳስ አፍቃሪዎችን ትኩረት ስቧል።

ያማል የባርሴሎና የሊግ ተቀናቃኝ የኾነው ሪያል ማድሪድ በሚጫወትበት ወቅት ጨዋታቸውን የሚከታተለው ማድሪዶች እንዲሸነፉ እየተመኘ እንደኾነ ነው የጠቆመው።

በሌላ በኩል የጀርመኑን ባየርን ሙኒክ ጨዋታ መመልከት እንደማይመቸው የገለጸው ያማል፣ ምክንያቱ ደግሞ ቡድኑ በጨዋታዎች ላይ የሚያሳየው ፍጹም የበላይነት ጨዋታውን አሰልቺ ስለሚያደርገው እንደኾነ ገልጿል።

የወጣቱ አጥቂ ግልጽና ደፋር አስተያየት በስፔን ስፖርት መገናኛ ብዙኀን እና በደጋፊዎች ዘንድ ትልቅ መነጋገሪያ ኾኗል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_11_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here