የ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በለንደኑ ደርቢ ብሬንትፎርድ ከቼልሲ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል።
ካለፉት ሁለት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ያገኘው ቼልሲ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ በሚያደርገው ጥረት፣ እስካሁን ምንም ጨዋታ ካልተሸነፈው ብሬንትፎርድ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል።
የተከላካይ ክፍሉን ችግር መቅረፍ ያልቻለው ቼልሲ፣ ከሜዳው ውጪ ምሽት 4:00 ላይ በሚያደርገው ጨዋታ የአማካዩን ሞይሰስ ካይሴዶን ግልጋሎት በጉዳት ምክንያት የማያገኝ ሲኾን ማርኮ ፓሌስትራ እና ጆርዳን ሄንደርሰንም በተመሳሳይ ምክንያት ከሥብሥቡ ውጭ ኾነዋል።
ዦአኦ ፔድሮ በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ውጭ ቢኾንም በምሽቱ ጨዋታ ግን የሥብሥቡ አካል ሊኾን እንደሚችል ተዘግቧል።
በብሬንትፎርድ በኩል ጆሽዋ ዳሲልቫ እና ናታን ኮሊንስ በጉዳት የማይሰለፉ ተጫዋቾች ናቸው ሲል ስካይ ስፖርት አስነብቧል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_08_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



