አትሌት ልቅና አምባው እና አለሽኝ ባወቀ የወርቅ ሜዳሊያ ግምት ያገኙበት የኮፐንሃገን የ5 ኪሎ ሜትር የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ።

0
89

 

43 የዓለማችን ምርጥ አትሌቶች ለሀገራቸው ክብር በሚፋለሙበት የኮፐንሃገን የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በጉጉት እየተጠበቀ ነው።

በዚህ ውድድር ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ልቅና አምባው እና አለሽኝ ባወቀ ከፍተኛ የአሸናፊነት ቅድመግምት አግኝተዋል።

ዓመቱን ሙሉ በዳይመንድ ሊግ አስደናቂ ብቃት ስታሳይ የቆየችው እና በቡዳፔስት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ አልቲሜት ሻምፒዮና በ5000 ሜትር አሸናፊ የኾነችው ልቅና አምባው ቅዳሜ መሥከረም 9/2019 ዓ.ም ከሰዓት 9፡10 ላይ በሚካሄደው የሴቶች 5 ኪሎ ሜትር ውድድር ተጨማሪ ድል ለማስመዝገብ ወደ ሜዳ ትገባለች።

ልቅና በሮም ዳይመንድ ሊግ ያስመዘገበችው 14 ደቂቃ ከ18 ሰከንድ ከ41 ማይክሮ ሰከንድ የዓመቱ ፈጣን ሰዓት ሲኾን በአሁኑ ወቅትም በዓለም የሴቶች 5000 ሜትር የደረጃ ሰንጠረዥን በበላይነት እየመራች ትገኛለች።

በሌላ በኩል በቡዳፔስት አልቲሜት ሻምፒዮና ተመሳሳይ ርቀት 5ኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው አለሽኝ ባወቀ ሌላኛዋ የማሸነፍ ቅድመ ግምት የተሰጣት አትሌት ናት። በዩጅን ዳይመንድ ሊግ በ2 ማይል ርቀት 9 ደቂቃ 20 ሰከንድ ከ02 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት የዓመቱ ፈጣን ሰዓት ባለቤት የኾነችው አለሽኝ፣ በማጠናቀቂያ ሜትሮች ባላት አስደናቂ ፍጥነት ምክንያት በሁለቱ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ከፍተኛ ፉክክር ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል።

በውድድሩ የርቀቱ ፈጣን የ5 ኪሎ ሜትር ሰዓት 14:19 ባለቤት የኬንያዋ ካሮላይን ኒያጋ እና ካሮላይን ጊቶንጋ፣ እንዲሁም በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወርቅ እና የነሐስ ሜዳሊያ ያስገኘችው የዩጋንዳዋ ቻሪቲ ቼሮፕ ዋና ተፎካካሪዎች ናቸው።

በተጨማሪም የኔዘርላንድሷ ዲያን ቫን ኤስ እና የቤልጂየሟ ያና ቫን ሌንት ጨምሮ በርካታ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሜዳሊያ ባለቤቶች በዚሁ ውድድር ይሳተፋሉ።

ኢትዮጵያ ከሦሥት ዓመት በፊት በሪጋ በተካሄደው ውድድር በአትሌት እጅጋየሁ ታየ አማካኝነት የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘቷ የሚታወስ ነው።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_08_2019_ዓ_ም

በሐናማርያም መስፍን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here