ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የካፍን ይሁንታ ያገኘው የባሕር ዳር ስታዲየም የአህጉሩን ታላቅ ጨዋታ መስከረም 19/2019 ዓ.ም ያስተናግዳል።
ከስታዲየሙ ዝግጅት በተጨማሪ የከተማዋ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና የፀጥታ አካላት ውድድሩን ለማከናወን ዝግጅት እያደረጉ ነው።
እንግዶቿን ሁሌም የምታከብረው ባሕር ዳር ከተማ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን አባላትን እና የእግር ኳስ ልዩ ፍቅር ያለውን ታዳሚ ጨዋታውን ታድሞ ድጋፉን እንዲሰጥ ለማስቻል ከወዲሁ እያዘጋጀች ትገኛለች።
ለዚሁም የክልሉ ባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና ከጸጥታ አካላት ጋር በመኾን የደኅንነት ማረጋገጥ ሥልጠና እየሰጠ ነው።
ሥልጠናው ወጣቶች እና በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የጸጥታ አካላት የባሕርዳርን እንግዳ ተቀባይነት እንዲያሳዩ ያስችላቸዋል ነው የተባለው።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_07_2019_ዓ_ም
በዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



