የሁለት ጊዜ የበርሊን ማራቶን አሸናፊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በርሊን ላይ ሊሮጥ ነው።

0
95

 

የሁለት ጊዜ የበርሊን ማራቶን አሸናፊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ መስከረም 27/2019 ዓ.ም. በሚካሄደው የ2026 የበርሊን ማራቶን ውድድር ላይ ከሌሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ኮከቦች ጋር እንደሚሳተፍ ተገልጿል።

በዓለም አትሌቲክስ አፍቃሪዎች ዘንድ ትልቅ ትኩረት በተሰጠው በዚህ ውድድር ቀነኒሳ በቀለ ወደ በርሊን መድረክ መመለሱ ዋነኛው አነጋጋሪ ርዕስ ኾኗል።

አትሌቱ በፈረንጆቹ 2019 በዚሁ ውድድር 2 ሰዓት 1 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በመሮጥ የግል ምርጥ ሰዓቱን ማስመዝገቡ ይታወሳል።

በወንዶች ዘርፍ ከቀነኒሳ በተጨማሪ የ2021 የበርሊን ማራቶን አሸናፊው ጉዬ አዶላ (2:03:46)፣ ጌታነህ ሞላ (2:03:34)፣ ሹራ ኪታታ (2:03:59) እና ደጀኔ ኃይሉ (2:04:15) ለመሳተፍ እንደተዘጋጁም ተገልጿል።

እንዲሁም ሰለሞን ባረጋ፣ ታረሳ ቶሎሳ፣ ታዱ አባተ እና አሰፋ ቦኪ ሀገራቸውን ወክለው ይሮጣሉ።

በሴቶች ምድብ ደግሞ በዳቱ ሂርፓ፣ ደራ ዲዳ፣ ዘይነባ ይመር፣ ምሥጋና ዓለማየሁ እና በቀለች ጉዴታ ለአሸናፊነት እንደሚሮጡ ታውቋል።

ለኢትዮጵያውያን ሯጮች ልዩ ትርጉም ባለው በዚህ ውድድር ቀነኒሳ በቀለ በድጋሚ በበርሊን ታሪክ ይሠራል ወይስ የወጣቶቹ ኮከቦች የበላይነት ይጎላል የሚለው በትልቅ ጉጉት ይጠበቃል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_07_2019_ዓ_ም

በዳናይት ሲሳይ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here